
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ባለሃብቶች 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ሲሆን ለ 4 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥሩ ተገልጿል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ግርማይ ልጃለም እንደተናገሩት 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ በምግብ ነክ፣ በቴክስታይል፣ በኬሚካል፣ በብረታ ብረት ዘርፍ የሚሰማሩ ሲሆን በቀጣይ ለ4 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል። ከ46 ባለሃብቶች መካከል 10ሩ ዲያስፖራዎች መኾናቸውን አቶ ግርማይ ገልጸዋል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ ከተማችን እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጭ ያላት ከተማ ስትኾን ጸጋዎቿን በመለየት ኢንቨስት ማድርግ ይገባል ብለዋል፡፡ ከተማ አሥተዳደሩ ባለሃብቶች ወደ ሥራ ሲገቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡ ባለሃብቶች የተሰጡት በኢንዱስትሪ መንደር ቁጥር 5 መኾኑም ታውቋል።
መረጃው፡- የጎንደር ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!