ኢትዮጵያ እና ሊቢያ በቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ዙሪያ መክረዋል።

53

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዳባቢ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሊቢያ አቻቸውን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዳባቢያን በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት በቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት፣ ምጣኔ ሃብታዊ ትብብር፣ የሰው ኃይል ልውውጥ እና በሌሎች የጋራ ፍላጎቶች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል የፈተና የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ኾነ፡፡
Next articleድርቅን መቋቋም የሚቻለው በምንድን ነው?