የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ተመለከቱ።

29

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እያከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት አምስት ክፍለ ከተሞችን ያካለለ ነው። በዚህ የኮሪደር ልማት በተለይ ከፒያሳ እና ሌሎች አካባቢዎች የተነሱ ነዋሪዎች የግል ይዞታ፣ የቀበሌ ቤት እና ኪራይ ቤቶች ውስጥ የነበሩ ነዋሪዎች የተለያዩ ምርጫዎች ቀርበውላቸዋል ነው የተባለው።

በዚህም ምትክ ኮንዶሚኒየም ባለአንድ መኝታ፣ የመንግሥት ቤቶች ልማት ያሠራቸው አፓርታማዎች ላይ በኪራይ ውል እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላትም በሐና ፉሪ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እና በፈረንሳይ ጉራራ ቤት የተሰጣቸውን የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የማኅበራዊ መሠረተ ልማቶችን ከሞላ ጎደል በፍጥነት ለማሟላት ከተማ አሥተዳደሩ ጥረት እያደረገ እንደኾነ መመልከታቸውን አባላቱ ተናግረዋል። ሁሉም በሂደት ይሟላላቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸውም አባላቱ ገልጸዋል። ተነሺዎቹ ለልማት እየከፈሉ ያሉት መሥዋዕትነት አለ አሁንም ቀሪ መሠረተ ልማቶቹ እስኪሟሉ በትዕግሥት እንዲጠብቁ አባላቱ አደራ ብለዋል።

እስካሁን ከ2ሺህ 800 በላይ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች መኖራቸው ከከተማ አሥተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግሥቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሐሰተኛ ሰነድን በመጠቀም የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መኾኑን የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ።
Next articleበወልድያ ከተማ አሥተዳደር የተቋቋመው የከንቲባ ችሎት የነዋሪዎችን የዓመታት ቅሬታ እየፈታ ነው።