የአማራ ክልል ክፍተኛ መሪዎች የልዑካን ቡድን በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ “የሠላም፣ ፍትሕና ዕድገት ለኢትዮጵያ ሕብረት” አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ

25

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በውይይቱ በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም በሠላም፣ በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ በሽግግር ፍትሕ ዙሪያና በኢንቨስትመንትና ልማት ዙሪያ ሠፊ ምክክር ተካሂዷል።

የልዑክ ቡድኑ ከህብረቱ አመራሮች ጋር በሀገራችን እና በክልላችን ዘላቂ ሠላም ለማምጣት ቅድሚያ ሕግ ማስከበር የመንግሥት ኃላፊነት እንደሆነ፤ ከሕግ ማስከበር ጎንለጎን የሠላም እጆች ተዘርግተው ሁሉንም የሠላም አማራጮች በመጠቀም ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሠንግሥት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ለወኪሎች አብራርተዋል።

በቀጣይም የተሟላ ሰላም እንዲመጣ በማድረግ ኢትዮጵያዉያን እና ትውልደ ኢትዮጵዊያን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሰማራት ለሀገራቸው እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ከኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ወኪሎቻቸው ጋር በተለያዩ መንገዶች የሚደረገው ውይይትና የልዑክ ቡድኑ የሥራ ጉዞ እንደቀጠለ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በ29 ከተሞች በይፋ አስጀመረ፡፡
Next articleችግር ፈችው የቀለም ቀንድ!