ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በ29 ከተሞች በይፋ አስጀመረ፡፡

38

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፍሬህይዎት ታምሩ እንደተናገሩት የዲጅታል መታወቂያው በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም 90 ሚሊዮን ለሚኾኑ ዜጎች ለማዳረስ የታቀደ ነው። ኢትዮ ቴሌኮም በወር በአማካይ 1 ሚሊዮን ዜጎችን በመመዝገብ 32 ሚሊዮን ዜጎችን ተደራሽ በማድረግ የሀገራዊ እቅዱን 36 በመቶ የሚያከናውን ይኾናል ሲሉ ሥራ አሥፈጻሚዋ ተናግረዋል።

ብሔራዊ የዲጅታል መታወቂያ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጅን ዕውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች አንዱ መኾኑን ሥራ አሥፈጻሚዋ ተናግረዋል። አዳዲስ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለዜጎች ለማቅረብ፣ የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት፣ የፋይናንስ አካታችነትን የሚጨምሩ አነስተኛ የብድር አገልግሎቶችን ያለ ዋስትና ለማቅረብ፣ የዜጎችን ኑሮ ለማዘመን የሚያስችል መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ለዜጎች ፈጣን እና ሰዓት ቆጣቢ የኾነ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ሥራ አሥፈጻሚዋ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleማንዚ 15/2016 ም.አ ቺርቤዋ ጋዚቲ
Next articleየአማራ ክልል ክፍተኛ መሪዎች የልዑካን ቡድን በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ “የሠላም፣ ፍትሕና ዕድገት ለኢትዮጵያ ሕብረት” አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ