
አዲስ አበባ: ሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ትኩረቱን በአየር ንብረት ለውጥ፣ ግብርና እና ቴክኖሎጂ ላይ ያደረገ በብሪክስ ጥምረት ማዕቀፍ ስር የኢትዮጵያ እና የሩሲያ የምሁራን እንዲሁም የተመራማሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ኢትዮጵያ ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ የብሪክስ ጥምረትን መቀላቀሏም በብዙ መንገድ ተጠቃሚ ያደርጋታል ነው ያሉት።
በጉባኤው የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ምሁራን እንዲሁም ተመራማሪዎች የተገኙ ሲኾን የሩሲያን እና የኢትዮጵያን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚጠቅምም ተገልጿል።
ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!