የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የልዑካን ቡድን ከቴክኖሎጂ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ምክክር አድርገዋል።

41

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የልዑክ ቡድኑ ትልልቅ የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች በሀገራችን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ በዌስት ቨርጂኒያ ግዛት ከሚገኙ የኤሌክትሮኒክስ፣ ኢነርጂ እና የተለያዩ ቴክኖሎጅ አማራች የሆኑ እንዱስትሪ መሪዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ በሞርጋንታውን ኢንዱስትሪ ፖርኩ የሚገኙት ድርጅቶች የቴክኖሎጅ ሽግግር ለማድረግ፣ የሥራ እድል መፍጠር እና ለውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት የሚያስችሉ ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ በልዑክ ቡድኑ ገለጻ እና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።

የካምፓኒ መሪዎቹም የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የሰጡት መረጃ ያለውን ምቹ ሁኔታ መረዳት እንዲችሉ እንዳደረጋቸውና ወደ ኢትዮጵያ በመሄድም ኢንቨስትመንት ላይ እንደሚሠማሩ ፍላጎታቸውን ገልጸዋል። መንግሥት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የሚያሳድግ ፖሊስ እየተገበረ በመሆኑ በኢትዮጵያ ለዘርፉ የሚሆን የተማረ የሰው ኃይል በመኖሩ እና ኢትዮጵያ የአፍሪካ ገበያ በር ስለሆነች ካምፓኒዎች በሚሰማሩበት ኢንቨስትመንት ውጤታማ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በተያያዘም የልዑክ ቡድኑ ከዌስት ቨርጅኒያ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር በልዩ ልዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ውይይት ያደረገ ሲሆን ሀገር ቤት ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመሆን የምርምር እና ጥናት ሥራዎችን ለመጀመር መግባባት ላይ ተደርሷል። የከፍተኛ መሪዎቹ የልዑክ ቡድን የሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉዞ እንደቀጠለ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከር እና ለአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ በቁርጠኝነት እየተሠራ መኾኑን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር አሳወቀ።
Next articleከ9 ሺህ በላይ ሥራ ፈላጊዎችን ከሥራ ጋር ማገናኘት መቻሉን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡