
አዲስ አበባ: ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የገቢ አሠባሠብ ሂደቱን የሚያዘምን ዲጂታል የግብር ሥርዓት መገንባት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፋዊ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በዓለም ባንክ እና በገቢዎች ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው ውይይት ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ተወካዩች ተገኝተዋል።
ውስብስብ የነበረውን የግብር አሠባሠብ ሂደት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ወደ ዲጂታል መቀየር የቻሉት ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳ እና ኬኒያ ተሞክሯቸውን በመድረኩ አካፍለዋል። የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እንደ ሀገር ያለውን ለመጭበርበር የተጋለጠ የግብር አሥተዳደር ሥርዓት ዲጂታል በማድረግ ሀገር የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ይሠራል ብለዋል።
የዓለም ባንክ ለዚህ ዲጂታል የግብር አሥተዳደር ሥርዓት መገንባት የሚያግዙ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ በጋራ ለመሥራት ፍላጎት ማሳየቱንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!