
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 በተደረገው የክትትል ኦፕሬሽን ከተያዘው 2 ሺ 500 የኤ ኬ ኤም ጥይት በተጨማሪ ዘጠኝ ካዝና፣ የመሣሪያ መጠገኛ እና ሌሎች መሰል ቁሳቁሶች ለጽንፈኛው ሲጓጓዙ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የጎጃም ኮማንድፖስት መረጃ ከዚህ ቀደምም የሕብረተሰቡን ሰላም ለማናጋት ሲጓጓዙ የነበሩ 5 ሺ ጥይት፣ 32 ቦምብ እና ሌሎች ለሽብር ሥራ የሚውሉ ቁሳቁሶች ለጽንፈኛው ቡድን ከመድረሳቸው በፊት የማክሸፍ ግዳጆችን ሲወጣ ቆይቷል።
ጽንፈኛው ቡድን በከተማ የሽብር ሥራዎችን ለመፈጸም ቦምቦችን እና ጥይቶችን ከያለበት እያፈላለገ እንደሚገኝ ስለታወቀ ይህንን የሚያመክን የክትትል እና የአሰሳ ግዳጆች ወደፊትም አጠናክሮ በመቀጠል የሕዝብ ደኅንነት የመጠበቅ ተልዕኮው ይቀጥላል ሲል የጎጃም ኮማንድፖስት አሳውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!