“ኢትዮጵያ የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን ለማዘጋጀት የተሰጣትን አፍሪካዊ ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ ናት” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

34

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን – አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ሀሳብ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጭው መስከረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ዛሬ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሔራዊ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ የመክፈቻና የግንዛቤ መስጫ መድረክ ማካሄዳቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ታሪካዊት፣ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ኅብረት መስራች ሀገር ይህንን ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት የሚጠበቀውን የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክ ለማዘጋጀት የተሰጣትን አፍሪካዊ ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ ተግባብተናል ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሕጻናትን መቀንጨር ለመከላከል ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የአስተሳሰብና የአመጋገብ ሥርዓት ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን
Next articleየግብርና ባሕል እየኾነ የመጣው የበጋ መስኖ ልማት!