የደብረ ብርሃን ከተማ መዋቅራዊ ፕላን የነዋሪዎቿን ፍላጎት ከግንዛቤ ያስገባ እንዲኾን እየሠራ መኾኑን አሥተዳደሩ አስታወቀ።

14

ደብረ ብርሃን: ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት እየተሠራ ያለውን አዲስ መዋቅራዊ ፕላን ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመኾን እየገመገመ ነው። መዋቅራዊ ፕላኑ ለከተማዋ ለነዋሪዎች ተስማሚ እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀምም ቢሆን ሞዴል እንድትኾን ታስቦ እየተሠራ ስለመኾኑም ተነግሯል።

በ2027 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተመራጭ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም እና የንግድ ከተማ ለማድረግ ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑም ተመላክቷል። በቀጣይ ይተገበራል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን ሲተገበር የነዋሪዎችን የመሬት ፍላጎት፣ የቅርስ ጥበቃ እና የተለያዩ ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ከግንዛቤ ያስገባ እንዲኾንም ተሳታፊዎቹ ጠይቀዋል።

ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን ቆየት ብለን እናደርሳለን።

ዘጋቢ፡- አበበች የኋላሸት

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በ2016 ዓ.ም ዘጠኝ የሰብል ዝርያዎችን አጸድቀናል” የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
Next article“የሕጻናትን መቀንጨር ለመከላከል ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የአስተሳሰብና የአመጋገብ ሥርዓት ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን