“ውይይቱ ለቀጣይ የሥራ እቅዳችን መሠረት ነው” ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ.ር)

28

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ በውኃ እና ኢነርጂ ላይ ትኩረት አድርገው ከሚሠሩ አጋር የልማት ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ.ር) በንግግራቸው ውይይቱ በቀጣይ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በውኃ እና ኢነርጂ ዘርፍ በጋራ ስለምንሠራቸው ሥራዎች ውይይት ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡ “ውይይቱ ለቀጣይ የሥራ እቅዳችን መሠረት ነው” ብለዋል።

በተጨማሪ ውይይቱ እና ምክክሩ ለመማማር እድል የሚፈጥር እና ልምድ ለመለዋወጥ የሚያስችል መኾኑንም ኢንጅነር ሀብታሙ ጠቁመዋል፡፡ የፕሮጀክቶችን እቅድ ክንውን እና አፈጻጸም በጋራ ለመከታተል፣ ለመደጋገፍ እና አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንዲኹም የሥራ ጥራትን ለመከታተል እድል የሚፈጥር መድረክ መኾኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍን ሊያጸድቁ እንደሚገባ ተጠየቀ፡፡
Next article“ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን ተሰልፈን የአካባቢያችንን ሠላም እንጠብቃለን” የጭስ ዓባይና አካባቢው ነዋሪዎች