ሠርቶ መኖር እና መለወጥን እንጅ አልባሌ ሁከት እና ትርምስን እንደማይፈልጉ የማንኩሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

18

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን የማንኩሳ ከተማ ነዋሪዎች ከምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት አመራሮች ጋር በሰላም፣ ልማት እና የአፈር ማዳበርያ ስርጭት ዙሪያ ምክክክር አድርገዋል። በውይይቱ የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች የማንኩሳ ሕዝብ ሠርቶ መንኖርን እንጂ አልባሌ ትርምስ እና ሁከትን አይፈልግም ብለዋል። የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች እናስመልሳለን በሚል ሰበብ ዘረፋ እያካሄደ የሚገኝ ኃይል መኖሩንም ጠቅሰዋል። በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት በዚህ አግባብ የሚፈታ ጥያቄ የሌለ መኾኑን አውቀው በሰላማዊ መንገድ ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ነዋሪዎቹ ማንኛውም ጥያቄ እና አለመግባባት በውይይት ብቻ መፈታት አለበት፤ የእኛን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ ሳይታክት ቀን ከለሊት እየለፋ ያለው መከላከያ ሠራዊታችን ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባዋል በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ እና የኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ በክልሉ እና በዞኑ የተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ያስከተለው የሰውና የንብረት ዉድመት መሆን ያልነበረበት ነበር ብለዋል። ጦርነት በየትኛውም አግባባብ ውጤታማ መፍትሔ መሆን ስለማይችል ኅብረተሰቡ በሰከነ አግባብ ተደራጅቶ አከባቢውን እንዲጠብቅና ማንኩሳ ከተማ ወደ ቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ ከሠራዊቱ ጎን እንዲሠለፍ ጠይቀዋል ።

ጎጃም ኮማንድ ፖስት መረጃ እንደሚያመላክተው በዉይይቱ ላይ የምዕራብ ጎጃም ዞን እና የጃቢ ጠህናን ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ የግብርና ዘርፉን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራች መኾኗ ተገለጸ።
Next articleየኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ 28 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ለውጪ ገበያ አቀረበ፡፡