በ2016 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2.16 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገለጸ።

26

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ታደሰ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት ወደ ውጪ ከተላኩት ምርቶች 2.16 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በስምንት ወሩ ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ በዋናነት ከግብርና ምርቶች፣ ከአምራች ዘርፉ፣ ከማዕድን እና ከሌሎች ምርቶች መኾኑ ተገልጿል። አፈጻጸሙ ከእቅዱ አንጻር 69 በመቶ መኾኑን የጠቆሙት አቶ ተስፋየ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸርም የ164.18 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አለው ብለዋል።

የጫት ኬላዎች መበራከት እና ተደራራቢ ታክስ እና ቀረጥ መኖር፣ በድርቅ ምክንያት የቁም እንስሳት አቅርቦት እጥረት መከሰት፣ ኮንትሮባንድ እና ሕገ ወጥነት ለወጪ ንግድ መዳከም ምክንያቶች እንደነበሩ ተገልጿል። የኢፕድ መረጃ እንደሚያመለክተው አዳዲስ ምርቶችን ወደ ወጪ ንግድ ሥርዓቱ ለማስገባት፣ የወጪ ንግዱ ከሕገ ወጥነት ተላቅቆ በሕጋዊ የአሠራር ሥርዓት ብቻ እንዲመራ ለማድረግ እንዲሁም የወጪ ንግድ ምርቶችን ብዝኃነት እና ጥራት ለመጨመር ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑንም አቶ ተስፋየ ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ የሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ዓባላት የቀጣናውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ እየሠሩ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleበስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር መቻሉን የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።