
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ የሚመራው የሉዑክ ቡድን በላስ ቬጋስ ከተማ ዓመታዊ የቴክኖሎጅ ሲምፖዚም እና ኤግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
በቆይታው ለክልሉ ልማት ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን እና በዘርፉ ያለውን እድገት ለመገንዘብ የተቻለ መሆኑ ተገልጿል።
ከኤግዚቢሽን እና ሲምፖዚየሙ ጎን ለጎን ለክልሉ ልማት አጋዥ ከሆኑ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጅ አምራች ካምፓኒ መሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል። በቀጣይ አብሮ ለመሥራትም መግባባት ላይ ተደርሷል።
የሉዑኩ ከፍተኛ መሪዎች በቆይታቸው በላስ ቬጋስ እና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በክልሉ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ምክክር እና ውይይትም አድርገዋል።
የልዑኩ የሥራ ጉብኝትም የሚቀጥል መሆኑ ታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!