ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በሲዳማ ክልል የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ሥራዎችን ጎበኙ።

66

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጉብኝቱ ላይ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች እና የከተማ አሥተዳደሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም በይፋ ካስጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በተከናወኑ የንብ ማነብ፣ የወተትና የዶሮ መንደር ምስረታ ክልሎች ተጨባጭ ለውጥ አምጥተዋል።

የሲዳማ ክልልም በመርሐ ግብሩ እንደ ክልል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ስምንት ኢኒሼቲቮችና 68 ፓኬጆች አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቶ ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል። ዘገባው የፋና ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
Next articleየአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የሉዑክ ቡድን በሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።