
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሐዋሳ ገብተዋል፡፡
ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ሐዋሳ ሲገቡ የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ደስታ ሌዳሞ እና የክልሉ የሥራ ኀላፊዎች በሐዋሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ የሥራ ኀላፊዎቹ በቆይታቸው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!