የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሚደግፍ የመግባቢያ ሰነድ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) ጋር ተፈረመ፡፡

28

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) ጋር የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሚደግፍ የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴን ተግባራዊ በማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ፕሮጀክት ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚቆይ የቴክኒካል፣ የፖሊሲ እና የአቅም ግንባታ ድጋፎችን እንደሚያካትት ተጠቁሟል፡፡

ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የእውቀት፣ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፎችን ከኤጀንሲው እንጠብቃለን ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ይህም የእወቅት እና የቴክሎጂ ሁኔታ በእድገት እና ተወዳዳሪነት ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ በመኾኑ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዋና ተወካይ (ወክለው ስምምነቱን የፈረሙት) ኬንሱኬ ኡሺማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማምጣት ከጀመረቻቸው እንቅስቃሴዎች መካከል በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት የጀመረችውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አንዱ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ንቅናቄውን እንደሚደግፉ እና አስፈላጊውን የእውቀት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡

እንደ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትን፣ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሠማሩ የግል ባለሃብቶች እና ማኅበራትን የማጠናከር አቅም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፍትሐዊ የመንገድ ተደራሽነት ጥያቄዎችን በዘላቂነት የሚፈታ የመንግድ ልማት ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሐዋሳ ገቡ፡፡