ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርእይን ጎበኙ።

39

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርእይን ጎበኙ።

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ተገኝተዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በአውደ ርእዩ በመጀመሪያ ደረጃ በምርት ሙከራና ምርት ወደ ገበያ ማቅረብ የጀመሩ ስታርት አፖች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

መጋቢት 30/2016 ዓ.ም የተከፈተው የስታርት አፕ አውደ ርዕይ እስከ ሚያዚያ 20 ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ኾኖ ይቆያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleቀጣናዊ ችግሮች እንዲፈቱ ኢትዮጵያ ከወዳጅ ሀገራት እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እንደምትሠራ ተገለጸ።
Next articleየለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።