
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን እና ፍላጎቷን መሰረት ያደረገ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን ታራምዳለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ካላት መልክዓ ምድራዊና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር አኳያ የቀጣናው ቀውስ ቀጥተኛ ተፅእኖ እንደሚያሳድርባት ተናግረዋል። በመኾኑም ችግሮች እንዲፈቱ ከወዳጅ ሀገራት እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እንደምትሠራ ገለጸዋል።
በሰላም ዕጦት ውስጥ ያሉ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ሰላም እንዲረጋገጥም አበክራ እንደምትሠራም ተገልጾል።
ኢዜአ እንደዘገበው በጎረቤት ሀገራት ሰላም እና መረጋጋት እንዲፈጠር በታሪክ የነበራትን የሰላም ማስከበር ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥልም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!