በምግብ ራስን ለመቻል በእንሰሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ላይ ሁሉም በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ።

22

ደሴ: ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምግብ ራስን ለመቻል ሁሉም አካል የእንሰሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ላይ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ የአማራ ክልል እንሰሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ጽሕፈት ቤት ገልጿል። ጽሕፈት ቤት በኮምቦልቻ ከተማ ለሦስት ቀናት ሲሰጠው የነበረውን የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ፓኬጅ የአሠልጣኞች ሥልጠናን አጠናቅቋል።

ሥልጠናውን የወሰዱ ባለሙያዎች የወሰዱት ሥልጠና የተሻለ ዕውቀት ያገኙበት እና አርሶ አደሮች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ምርት እና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር አዲስ ነገር ይዞ የመጣ እንደኾነም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል እንሰሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ ነጋ ይስማው ሥልጠናው ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ አሠራርን ተከትለው ውጤታማ እንዲኾኑ ታሳቢ ተደርጎ የተሰጠ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ በዘርፉ ምሁራን ለዘመኑ ተስማሚ ተደርጎ የተቀረፀ የሥልጠና ፓኬጅ በመኾኑ ለሙያተኞች ትልቅ አቅምን ይፈጥራል ነው ያሉት። ምክትል ኀላፊው ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ እና በምግብ ራስን ለመቻል ሁሉም አካል የእንሰሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዘጋቢ፡- መስዑድ ጀማል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አሥተዳደራዊ ፍትሕ የማኅበራዊ ፍትሕ የማዕዘን ድንጋይ ነው” አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
Next article“ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የማይበገር ምቹ አካባቢን በመፍጠር ለትውልድ ማስረከብ ይገባል” ከንቲባ አዳነች አቤቤ