
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጃይካ፣ ሳፋሪኮም እና ሱሚቶሞ ጋር በመተባበር የ10 ሺህ ዜጎችን አቅም የሚያጎልበት እና ግብርና ላይ ያተኮረ የብድር አሰጣጥ ሞዴልን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የፕሮጀክት ዕቅድ ላይ ምክክር አድርጓል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ በዲጂታል እና ውጥን/ስታርታአፕ /ኢትዮጵያ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሠራን ባለንበት ወቅት ከጃይካ፣ ሳፋሪኮም እና ሱሚቶሞ ጋር መሥራታችን ዘርፉን ስኬታማ ለማድረግ ያግዛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!