የብረት ምርትን ማሳደግ የሀገሪቷ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ አካል መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።

45

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የብረት ምርትን ማሳደግ የሀገሪቷ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ አካል መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ የኤሌትሪክ ገመዶችን እና የኤሌትሪክ ማማዎች በትኩረት እየተመረቱ ነው ብለዋል።

ዘርፉ ለኤሌክትሪክ ብሎም ለቴሌኮም ዘርፎች የሚውለውን ግብዓት በሀገር ውስጥ ማቅረብን ያለመ ነው ብለዋል።

የተሽከርካሪዎችን እና የመለዋወጫዎችን የምርት ሥራ በመመልከቴም ተደስቻለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከትም በእጅጉ ያበረታታል ነው ያሉት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እንደ ሀገር ለጀመርነው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ ፋይዳው የጎላ ነው” አቶ ተመሥገን ጥሩነህ
Next articleፊንላንድ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ቁርጠኛ መኾኗን ገለጸች፡፡