
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እንደ ሀገር ለጀመርነው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት የፕሮግራሙ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ገምግመንም ገልጸዋል፡፡
በቀሪ ወራት መፈጸም ያለባቸው ተግባራትን ተለይተዋል ነው ያሉት። በዚህ መሰረት በዓመቱ ለማሳካት የታቀዱ ተግባራትን በተሟላ መልኩ ለመፈጸም ከፕሮግራም ጽሕፈት ቤቱ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሚንስትሮች እና የተቋማት ኀላፊዎች ጋር የጋራ መግባባት መፈጠሩን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አሳውቀዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!