የአማራ ክልል በወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና መልካም አሥተዳደር ሥራዎች ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

73

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የክልሉን ወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና መልካም አሥተዳደር ሥራዎች የግምገማ መድረክ በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን እንደገለፁት መድረኩ በተለያዩ ጊዜያት የተነሱ የሕዝብ ጥያቄዎች በምን አግባብ እየተመለሱ ነው፤ አሁናዊ የሰላምና ጸጥታ ሥራችን ያለበት ደረጃ፣ አመራሩ የተሰጠውን ተግባር በዲፕሊን ከመፈጸም አኳያ ያለበት የአፈጸጸም ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ክልላዊ ተግባራትን እንደሚገመግም ገልጸዋል፡፡

በክልላዊ የግምገማ መድረኩ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) የመወያያ ጽሑፍ አቅርበው ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰላም እና ሥራ ማግኘት የእኛ መዳኛችን ነው፣ ከዚያ ውጭ ግን የምንጎርሰውም የምናጎርሰውም እናጣለን” የኑሮ ውድነት የፈተናቸው እናት
Next article“ስንፍና ቀለብ አይኾንም” አርሶ አደር አለሙ