
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚኾነውን አስመልሻለሁ ብሏል።
ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተፈጠረ ችግር ምክንያት 801 ሚሊዮን 417 ሺህ 747 ከ ከ81 ሳንቲም ያለአግባብ ተወስዶበት እንደ ነበር መገለፁ የሚታወስ ነዉ።
ከዚህ ገንዘብ ውስጥም 762 ሚሊዮን 941 ሺህ 341 ማስመለስ እንደቻለ ነው ያስታወቀው፡፡ ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ነዉ ብሏል ባንኩ።
ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ እንዳሰፈረው ቀሪውን 5 በመቶ የሚሆን ገንዘቡ የማስመለስ ሥራው እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
