
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በኢሚግሬሽን መረጃ ልውውጥ እና የድንበር ቁጥጥር ላይ ያላቸውን ትብብር ከፍ ለማድረግ ተስማምተዋል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሰይድ ኑህ ሀሰን ጋር በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እንዲሁም ከድንበር ቁጥጥር ጋር ተያይዞ ያሉ ትብብሮችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ሁለቱ ሀገራት በጅቡቲ በሚገኙ ሰነድ አልባ ዜጎች፣ በኢሚግሬሽን መረጃ ልውውጥ፣ በድንበር ቁጥጥር፣ በዜግነት አገልግሎቶች እና በጅቡቲ በሚኖሩ የመኖሪያ ፍቃድ ፈላጊ ዜጎች ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡
ክፍተቶችን በመለየት የነበሩ ትብብሮችን ይበልጥ ለማጠናከርም ተስማምተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
