የጀርመን መንግሥት ለስምንት ሆስፒታሎች የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

36

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጀርመን መንግሥት በጀርመን ልማት ባንክ አማካኝነት ለስምንት የማስተማሪያ ሆስፒታሎች የ 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። የሕክምና ቁሳቁሶቹም የትምህርት እና የጤና ሚኒስቴር የሥራ ኀላፊዎች፣ የጀርመን ልማት ባንክ ተወካይ፣ የጀርመን ኤምባሲ እና የሆስፒታሎቹ ኀላፊዎች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

ድጋፍ የተደረገላቸውም ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ፈለገ ሕይወትአጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል፣ አዳማ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ጂማ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ማዕከል፣ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል እና አርባ ምንጭ ሪፈራል ሆስፒታል ናቸው።

ለሆስፒታሎቹ ከሕክምና ቁሳቁስ በተጨማሪ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚደረግም ኢዜአ ዘግቧል። ጀርመን ለኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ እያደረገች ነው፡፡ በቀጣይም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባቲ ከተማና አከባቢው የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በትኩረት እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ።
Next articleከአዙሪት ያልተላቀቀው ህልም