
ደሴ: ሚያዚያ 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኮምቦልቻ ከተማ በአዲስ ዓለም አጸደ ሕጻናት ትምህርት ቤት ውስጥ በ20 ሚሊዮን ብር በጀት የሚገነባው የመማሪያ ክፍል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተደምሯል። ግንባታውን በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።
የቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር በኃይሉ አየለ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ የትምህርት ቤት ግንባታው ወደ ሥራ መግባቱን ጠቅሰዋል። የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታውን በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሠራም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ መንግሥቱ አበበ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቱ ግንባታ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት። የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድአሚን የሱፍ የመማሪያ ክፍሉ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከተማ አሥተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የከተማዋ ነዋሪዎችም የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍል ግንባታ በመጀመሩ ደስተኛ መኾናቸውን ነው የገለጹት።
ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
