
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በጎጃም ኮማንድፖስት ሥር የሚገኘው ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አበበ አደመ ፈረስ ቤትን ለመቆጣጠር በቅዥት አቅዶ የመጣው ጽንፈኛ ኃይል ተቀጥቅጦ ከመሞት እና ከመቁሰል የተረፈው ተንጠባጥቦ መፈርጠጡን ገልጸዋል።
በዚህ ውጊያ ሦስት የጽንፈኛው አመራሮችን ጨምሮ 64 ሲደመሰሱ፤ 47 ቆስለዋል።
ኮሎኔል አበበ እንዳሉት ፈረስ ቤትን ለመያዝ ጽንፈኛው ያለችውን ኃይል ከመራዊ፣ ከቋሪት፣ ከአዴት፣ ከሰከላ እና ከሞጣ አሰባስቦ በማምጣት ተኩስ ቢከፍትም በጀግኖቹ የሠራዊት አባላት እና የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ተቀናጅተው ባደረጉት ፀረ ማጥቃት ዘመቻ ሊመታ ችሏል።
ክፍለ ጦሩ በቀጣይም የሕዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሕግ የማስከበር ግዳጆችን በመፈጸም የተጣለበትን ኀላፊነት በብቃት መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አዛዡ አረጋግጠዋል።
መረጃው፡- የጎጃም ኮማንድፖስት ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
