የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 12 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ፡፡

36

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 12 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አድርጓል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ የተሽከርካሪ ድጋፉን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አስረክበዋል።

እንደ ኢዚአ ዘገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እና የተሳካ እንዲኾን ኮሚሽኑ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከጃፓን መንግሥት በድጋፍ የተገኙት ተሽከርካሪዎች ኮሚሽኑ በተለያዩ ክልሎች የሚያከናውናቸውን የመስክ ሥራዎች ለማቀላጠፍ ያግዛሉ ብለዋል። ኢትዮጵያ መሠረታዊ በሚባሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የዝግጅት ሥራዎችን በማካሄድ ላይ መኾኗንም ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ጃፓን ለኮሚሽኑ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
Next articleየአማራ ክልል አድማ ብተና አባላት ሕዝባቸውን ለመካስ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መኾናቸው አስታወቁ።