ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

39

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለሁለት ቀናት የሚቆየው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

በጉባኤው ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እና የዘርፉ ተመራማሪዎች እየተሳተፉ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ዛሬ እና ነገ በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ ላይ ከ37 የሚበልጡ ሀገራት እየተሳተፉ እንደሚገኝም ኢቢሲ ዘግቧል።

ጉባኤው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለንተናዊ ትብብርን በሚያጠናክር እና በሰላም ግንባታ እንዲሁም በዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ጉዳይች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪ ሀገራዊ ዕድሎች እና ፈታኝ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሄደ ነው።
Next articleየጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 12 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ፡፡