የማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪ ሀገራዊ ዕድሎች እና ፈታኝ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሄደ ነው።

26

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪ ሀገራዊ ዕድሎች እና ፈታኝ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። የምክክር መድረኩ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ትብብር የተዘጋጀ ነው።

በመድረኩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ.ር)ን ጨምሮ የክልል እና የፌዴራል የሥራ ኀላፊዎች፣ የማሽነሪ አምራች እና አቅራቢዎች እንዲሁም የኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና ሥራ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዕድሎች እና ፈታኝ ሁኔታዎች እንዲሁም ቀጣይ ሥራዎችን የሚያመላክቱ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየወልድያ ከተማን ጨምሮ የአጎራባች ወረዳዎችን ተስፋ ከፍ ያደረገው የጤና ተቋም ግንባታ!
Next articleሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።