በእነዋሪ ከተማ ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ አዲስ የዱቄት ፋብሪካ ግንባታ ተጀመረ፡፡

68

ደብረ ብርሃን፡ ሚያዝያ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ከተማ አሥተዳደር እንዳስታወቀው ባለቤትነቱ ኪዳሞስ አግሮ ኢንደስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የዱቄት ፋብሪካ በእነዋሪ ከተማ አሥተዳደር ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ እየተገነባ ይገኛል።

በዞኑ በትርፍ አምራችነታቸው ከሚጠቀሱ ወረዳዎች መካከል የሞረትና ጅሩ ወረዳ በስንዴ ምርት የሚታወቅ ነው፡፡

በ5 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው ይህ የዱቄት ፋብሪካ በአካባቢው በቂ የሆነ ምርት ያለ በመሆኑ ለአርሶ አደሩና ለሌላው ማኅበረሰብ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ እንደሆነ የከተማ አሥተዳደሩ ከንቲባ ሸዋንግዛው ደጀኔ ተናግረዋል፡፡

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቅቆ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹት ከንቲባው ለ250 ሥራ ፈላጊ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተጠቁሟል፡፡

ዘጋቢ፦በላይ ተስፋዬ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ ነው።
Next articleየግብርና ውል እርሻ በአስገዳጅ ሕግ እንዲቃኝ መደረጉ ለምርታማነት ማደግ አቅም እንደሚፈጥር ተመላከተ።