
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ መኾኑን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) አስታወቀ።
ማሽነሪዎቹ በሐረር መርከብ ተጭነው ጅቡቲ ወደብ መራገፋቸውን ያስታወሰው ኢባትሎ፤ አሁን ላይም በከባድ የየብስ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ ይገኛሉ ብሏል።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ በቀን ከ10 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ የማምረት አቅም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
ለሚ ሲሚንቶ በግንባታ ሒደት ላይ ኾኖ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲኾን ግንባታው ተጠናቅቆ ምርት ማምረት ሲጀምር ከ20 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር እንደሚችል የኢባትሎ መረጃ አመልክቷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!