በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የጉለሌ የተቀናጁ የልማት ሥራዎችን ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርቀው ከፈቱ፡፡

34

አዲስ አበባ፡ ሚያዝያ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የጉለሌ የተቀናጁ የልማት ሥራዎችን ነው መርቀው ሥራ ያስጀመሩት፡፡

በጉለሌ ከፍለ ከተማ የተገነቡ እና የተመረቁት ኘሮጀክቶች የምገባ ማዕከል፣ የመኖሪያ መንደር፣ የእንጀራ ፋብሪካ፣ የወተት ምርት ማዕከል እና የመንገድ ሥራ ናቸው።

ፕሮጀክቶቹ በእንጦጦ እና አካባቢዋ የሚገኙ ወጣት ሴቶች እና ወንዶች፣ አባቶች እንዲሁም እንጨት በመሸከም ኑሯቸውን ሲመሩ የነበሩ እናቶችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ነው የተባለው።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምግብ ብክነትን ማስወገድ እና ጥራትን ማስጠበቅ የሚያስችሉ ሦስት ሀገራዊ ስትራቴጂዎችን የግብርና ሚኒስቴር አስተዋወቀ፡፡
Next articleየእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ አሠራር አስተዋወቀ፡፡