
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በስዊዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በባዝል ከተማ ዉይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ በስዊዘርላንድ ባዝል ከተማ እኤአ ኤፕሪል 11/2024 በተካሄደው 3ኛው ዓለም ዓቀፍ የትብብር መድረክ ላይ ተሳትፈዋል። ከዚህ ጎን ለጎንም በስዊዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር ማጠናከርና ተሳትፏቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው ፕሬዝዳንቷ ገልጸዋል።
“እኛ ኢትዮጵያውያን የሰላምን ዋጋ መረዳትና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ማዳበር ይኖርብናል” ያሉት ፕሬዝዳንቷ ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል። በመድረኩ በጄኔቫ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቋሚ መልክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው፣ ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ ጋር በትብብር ለመሥራትና የዳያስፖራውን ሁለገብ ተሳትፎ ለማሳደግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!