
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጠው የቆዩ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ እየጀመሩ መኾኑን በምሥራቅ ጎጃም ዞን ትምሕርት መምሪያ ገልጿል። በዞኑ በተፈጠረዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረዉን ትምህርት ለማስጀመር ከወላጆች፣ መምህራንና ተማሪዎች፣ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው። በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የሚገኙ 33 የመጀመሪያ ደረጃ እና 5 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን መዝግበው ማስተማር ጀምረዋል።
በዞኑ ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት በሁሉም ወረዳዎች ለማስጀመር ባለፉት ሁለት ሳምንታት የንቅናቄ መድረክ ሲካሄድ ቆይቷል። 17 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 2 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራቸው መመለሳቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ መረጃ ያሳያል።
አሁን ወደ ማስተማር ሥራ የገቡት በአብዛኛዉ በከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሲኾኑ በገጠር የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ወደ ማስተማር እንዲገቡ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን መምሪያው ገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!