ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለመሠብሠብ እየተሠራ እንደኾነ ተገለጸ፡፡

25

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል አንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለመሠብሠብ እየተሠራ እንደኾነ ተገለጸ፡፡ በኢትዮጵያ ያጋጠመውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመቀልበስ በሚካሄደው የድጋፍ የማሠባሠቢያ ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና አጋር አካላት አረጋግጠዋል።

በፕሮግራሙ እንደሚሳተፉ የገለጹት እንግሊዝ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ አውስትራሊያ፣ ቤልጀየም፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ጣሊያን፣ ሉክሰምበርግ፣ ኔዘርላንድ፣ ኒውዝላንድ፣ ኖርወይ፣ ስዊድን እና አሜርካ ናቸው። ይህ የድጋፍ ማሠባሠቢያ ፕሮግራም ሚያዚያ 8/2016 በጄኔቫ ስዊዘርላንድ ይካሄዳል ነው የተባለው።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው ፕሮግራሙን የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እና የእንግሊዝ መንግሥት በጋራ የሚያዘጋጁት ሲኾን 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለመሠብሠብ መታቀዱን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለአጣዬ ከተማ እና አካባቢው ሰላም መኾን ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።
Next article“በሳይንስ ሙዚየም እየታየ ያለው የ’ስታርት አፕ’ ኢትዮጵያ አውደርዕይ በዘርፉ ያሉ ተሳታፊዎችን ተምኔት፣ የፈጠራ ምናብ ስፋት ብሎም ችሎታ ማሳያዎች ቀርበውበታል። ሁላችሁም አውደ ርዕዩን በመመልከት ከተሳታፊዎቹ ጋር እንድትወያዩ እጋብዛለሁ።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶር.)