የሁለቱ ዒድ እውነታዎች፡፡

33

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የሁለቱ ስያሜ በዒድ የሚጀምር ነው፡፡ ዒድ አል አድሃ እና ዒድ አልፈጥር በመባልም ይታወቃሉ። ዒድ ቃሉ አረበኛ ሲኾን ትርጉሙም በዓል፣ ድግስ፣ ዓመት በዓል እንደ ማለት ነው።

የዒድ አል አድሃ በዓል የመስዋዕትነት በዓል በመባል ይታወቃል። በዓመተ ሒጅራ አቆጣጠር መሠረት በመጨረሻው ወር 10ኛ ቀን ላይ ይከበራል። በዓሉ አሏህ የኢብራሒምን እምነት ለማረጋገጥ ልጃቸውን ኢስማኤልን እንዲሰውላቸው ትዕዛዝ የሰጡበት፣ ኢብራሂምም ልጃቸውን ኢስማኤልን ለመስዋዕትነት ያዘጋጁበት፣ ይሁን እንጅ በአሏህ ጣልቃ ገብነት በምትኩ በግ እንዲያርዱ ያደረጋቸውን ታሪክ ያስታውሰናል። ይህን በዓል የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ወደ መስጂድ በመሄድ እና ሰላት በመስገድ ያከብራሉ።

ዒድ አልፈጥር ዛሬ ኢትዮጵያን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ጨምሮ በመላው ዓለም እየተከበረ ያለው በዓል ነው። ይህ በዓል በዓመተ ሒጅራ አቆጣጠር መሠረት በ10ኛው ወር የመጀመሪያ ቀን የሚከበር ነው። እንደ ሀገራቱ ሁኔታ ከ 1 እስከ 3 ቀን ሊቆይ ይችላል። በዓሉ የታላቁ የረመዷን ወር መጠናቀቅን ተከትሎ ይከበራል።

የእምነቱ ተከታዮች ይህን የደስታ እና የበረከት በዓል በጸሎት፣ በስግደት፣ ድኾችን በመርዳት፣ ስጦታ በመለዋወጥ፣ ጣፋጭ ምግቦችን በማዘጋጀት እና በመመገብ ያከብሩታል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዒድ አልፈጥር በዓል ገጽታ በዓለም ዙሪያ
Next articleከ50 ዓመታት በላይ ሳያቋርጡ በሙአዚንነት ያገለገሉት ሼህ መሐመድ ከማል።