የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኀይል የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም መጠናቀቁን ገለጸ፡፡

28

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመላው ሀገሪቱ የተከበረው 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አልፈጥር በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኀይል ገልጿል። የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኀይል ሕዝቡን ከጎኑ በማሰለፍ ሰላም እና ደኅንነት የማስከበር ሥራውን በብቃት ተወጥቷል ብሏል።

በጸጥታው ባስከበር ላይ የተሰማሩት የጸጥታ አካላት ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከራሳቸው በፊት ሕዝቡን በማስቀደም የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የታለመውን ግብ አሳክተዋል ነው ያለው። ለዚህም የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኀይል ላቅ ያለ ምሥጋና እንደሚያቀርብም አብራርቷል።

መላው የሀገሪቱ ሕዝብም ከግብረ ኀይሉ የተሰጠውን መግለጫ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ላደረገው ቀና ትብብር እና ድጋፍም ግብረ ኀይሉ ምሥጋናውን አቅርቧል። ለዚህ ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡት የእስልምና እምነት ተከታዮች እና የሃይማኖት አባቶች፣ በዓሉን ላስተባበሩ እና ለመሩት ወጣቶች ላደረጉት ከፍተኛ ትብብር ምሥጋና እንደሚገባቸው ነው የገለጸው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የረመዷን ጾም ከምግብ እና ከመጠጥ ተዓቅቦ በላይም ነው”
Next article“ሰላምን በወደድን ጊዜ ፈጣሪ በእዝነት ዐይኑ ያየናል”