የአካባቢን ሰላም እና ደኅንነት በመጠበቅ ሕዝበ ሙስሊሙ የድርሻውን አንዲወጣ ተጠየቀ፡፡

20

ወልድያ: ሚያዚያ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በወልድያ ከተማ እየተከበረ ነው። የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ማህሙድ ኑርዬ በዓሉን በደስታ ከቤተሰቦቹ ጋር እያከበረ የሚገኘው የከተማዋ ሙስሊም ማኅበረሰብ በቤታቸው ማክበር ያልቻሉትን እንዲያስብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሼህ ማህሙድ “ከተለያየ አካባቢዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ ያሉ ወገኖች በመኖራቸው በዓሉን ስናከብር በመጠለያ እና ከመጠለያ ውጭ ያሉ ተፈናቃይ ወገኖቻችንን ታሳቢ አድርገን ሊኾን ይገባል” ብለዋል። የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ የከተማዋ ሙስሊም ማኅበረሰብ በወልድያ ልማት እና እድገት ጉልህ ድርሻ እንዳለው አንስተዋል።

ከተማዋ ሰላማዊ ትኾን ዘንድም የአካባቢን ሰላም እና ደኅንነት በመጠበቅ ሕዝበ ሙስሊሙ የድርሻውን አንዲወጣም አሳስበዋል።

ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለቢሮ ግንባታ ቦታ ከከተማ አሥተዳደሩ ተረከበ፡፡
Next article1ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በኮምቦልቻ ከተማ ተከብሯል፡፡