የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለቢሮ ግንባታ ቦታ ከከተማ አሥተዳደሩ ተረከበ፡፡

47

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር ለደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የቢሮ ግንባታ የሚኾን 500 ካሬ ሜትር ቦታ አስረክቧል፡፡

የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቱ መሀል ከተማ ላይ ነው ለቢሮ ግንባታ የሳይት ፕላን ቦታ የተረከበው፡፡ ቦታውን የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ አስረክበዋል፡፡

በርክክቡ ላይ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለጥያቄው መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ በመስጠቱ አመሥግነዋል፡፡ ደስታቸውንም ገልጸዋል፡፡ የደሴ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው በሰላት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙ አማኞች ጽንፈኛውን በማውገዝ ከመንግሥት እና ከለውጥ አመራሩ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዚህ ዓመት በረሃብ እና ግጭት ምክንያት በጋዛ፣ ሱዳን እና በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ሙስሊሞች በዓሉን በአግባቡ አለማክበራቸውን ሳስብ ልቤ ያዝናል” አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
Next articleየአካባቢን ሰላም እና ደኅንነት በመጠበቅ ሕዝበ ሙስሊሙ የድርሻውን አንዲወጣ ተጠየቀ፡፡