
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አቀፍ ተቋማት እና የሀገራት መሪዎች 1 ሺህ 445ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት እያስተላለፉ ነው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት በመላው ዓለም ለሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የዒድ አልፈጥር በዓልን በተመለከተ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ብለዋል።
ዋና ጸሐፊው “በዚህ ዓመት በረሃብ እና ግጭት ምክንያት በጋዛ፣ ሱዳን እና በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ሙስሊሞች በዓሉን በአግባቡ አለማክበራቸውን ሳስብ ልቤ ያዝናል” ብለዋል።
የሳኡድ አረቢያ ንጉስ ሰልማን እና አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን የዒድ አልፈጥርን በዓል አስመልክቶ ከሀገራት መሪዎች ጋር የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት ተለዋውጠዋል።
የሳኡዲው አረብ ኒውስ ጋዜጣ እንዳስነበበው ንጉሱ እና አልጋ ወራሹ በመልክታቸው ለዓለም ጸጥታ፣ መረጋጋት እና ብልጽግናን ተመኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!