ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዷን ወር የነበሩ በጎ ምግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው ተጠየቀ።

8

እንጅባራ: ሚያዚያ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በእንጅባራ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የቢላል መስጅድ ኢማም ሼህ አብዱ ቡሽራኽ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሼህ አብዱ በመልዕክታቸውም በረመዷን ወር የነበሩ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ በጎ ምግባራት ከበዓሉ በኋላም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ወቅቱ ሰላም የጠፋበት እና በርካታ ወገኖች ችግር ላይ የወደቁበት ነው ያሉት ሼህ አብዱ ሁሉም ወገን ለሰላም መትጋት እንዳለበትም ገልጸዋል።

የበዓሉ ታዳሚዎችም በዓሉን የተቸገሩትን በመጠየቅ እና ካላቸው በማካፈል በጋራ እንደሚያከብሩት ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article1 ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰሜን ወሎ ዞን አላማጣ ከተማ እየተከበረ ነው።
Next article“የዒድ አልፈጥር በዓል ውስጣዊ አንድነት የሚጠናከርበት፣ ሰላም እና ፍቅር የሚጸናበት በዓል ነው” አሸተ ደምለው