
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ ከተማ የ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል እየተከበረ ነው፡፡የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይ በሰቆጣ ከተማ አንዋር መስጂድ ተገኝተው እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው ዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋ።
በዓሉ የሰላም፣ የወንድማማችነት፣ የእህታማማችነት፣ የደመቀ አንድነት የምናዳብርበት እና የፍቅር እንዲኾንላችሁ እመኛለሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
የአንዋር መስጊድ ኢማም ሼህ መሐመድ አደም በበኩላቸው “ዒድ ማለት መደሰት ማለት ነው፤ ዒድ ማለት የአንድነት፣ የአብሮነት፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ በዓል ማላት ነው” ብለዋል፡፡
መረጃው፡- የዋግ ኽምራ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!