
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 445ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አልፈጥር በዓል በባሕር ዳር ከተማ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው። በሥነ ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ጀውሃር ሙሐመድ “እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ” ብለዋል።
በበዓሉ ዋዜማ ያጋጠመን ችግር ውስጣችንን የሚነካ ቢኾንም በመተከዝ እና በማዘን ሳይኾን “ፊታችንን ወደ አሏህ አዙረን ድዓዋ በማድረግ ለሰላም እንጸልይ” ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ምስኪኖችን መጠየቅ ብቻ ሳይኾን ከአሏህ ጋር አብረን ሃይማኖቱ እንደሚያዘው እየተረዳዳን መቀጠል አለብን ብለዋል።
በተፈጠረው አደጋ ያጣናቸው ወንድሞቻችንን ቤተሰቦች ድዓዋ በማድረግ እንድናጽናናቸው ሲሉ አሳስበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!