
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የምድረ ገነት ከተማ አሥተዳደር ቀበሌ ነዋሪዎች እና የከተማ አሥተዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች በመንግሥት እየተመዘገቡ ላሉ ለውጦች ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ ሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልእክት ለሀገር ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና የበኩላቸውን እንደሚወጡ ነው ያስገነዘቡት፡፡
በጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብ እና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገር እና ሕዝብ እንደማይኖርም ሰልፈኞቹ ተናግረዋል፡፡ የላቀ ሕዝባዊ ተሳትፎን ለኢትዮጵያ ብልጽግና በመጠቀም ሀገራቸውን ወደ ከፍታ ለማሻገር ከለውጡ አመራር ጋር በጽናት እንደሚቆሙም ነው የገለጹት፡፡
በምዕራብ ጎንደር ዞን የምድረ ገነት ከተማ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ጉዳች ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን የታደገ እና ህልውናን ማስቀጠል ያስቻለ እንደኾነ ሰልፈኞቹ አስረድተዋል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የአንድነት እና የጥንካሬ መገለጫ እንደኾነም ነው ያብራሩት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!