
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ በዓሉ ሲከበር በመቻቻል አብሮ የመኖር እሴት እንዲጎለብት፣ የመተባበር፣ የመደጋገፍ እና እርስ በእርስ የመከባበር መልካም ተግባር የበለጠ እንዲጎለብት ማድረግ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት፡፡
አቶ ይርጋ ሲሳይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት በተለይም በረመዷን ወር ሲፈጸሙ የቆዩትን የመተሳሰብ እና የመረዳዳት በጎ ተግባር ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደሚጠበቅም አብራርተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!