ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ሕዝበ ሙስሊሙ የራሱን መልካም አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ዋና አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ጥሪ አቀረቡ፡፡

48

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ በዓሉ ሲከበር በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣ በመረዳዳት፣ በመተዛዘን እና በአብሮነት መንፈስ ሊኾን እንደሚገባ ዋና አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

የሰላም ዕጦት ምክንያት የኾነውን የአክራሪነት፣ የሕገወጥነት አመለካከት እና ተግባርን መጠየፍ እና ማውገዝ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ዋና አፈ ጉባኤዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ሕዝበ ሙስሊሙ የራሱን መልካም አስተዋጽኦ እንዲያበረክትም አደራ ብለዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰራዊቱ የሕዝቡን ሰላም ለማምጣት እና ሕግ ለማስከበር ባደረገው ስምሪት ጽንፈኛው ቡድን ቆሞ የመዋጋት ቁመናውን አጥቷል” ጀኔራል አበባው ታደሰ
Next article“የዒድ አል ፈጥር በዓል ሲከበር ለአንድነት እና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት መኾን አለበት” አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር